Author Archives

TEAM

Copyright ©2020 TEAM | Powered by Networks for a Free Society.

የአማራ ክልል የጫት ቃሚወችን ቁጥር ለመቀነስ የያዘው ዕቅድ:- ከፍተኛ ቀረጥ መጣል!

(ናይሮቢ) ሰዎች በግል የሚፈጽሙትን ጎጅ የሚባሉ ነገሮች እንዳይጎዳቸው ለማቆም ወይም ሰዎች ሌሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ለማድረግ እና ድርጊቱን ለመቀነስ መንግስታት የክልከላ ሕግ ማውጣታቸው የተለመደ ነው። ይሁን እንጅ መንግስታት ጎጅ ድርጊቶችን ለመቀነስ ወይም ለማስቀረት የሚያወጧቸው ሕጎች ብዙ ጊዜ ውጤታቸው ተቃራኒ ሲሆን ይስተዋላል።ይህን ጽሁፍ የምጽፈው ሰሞኑን በአማራ ቴሌቪዥን ዜና ላይ የአማራ ክልል […]

ነፃነት እና ምግባር፡-የራስ እና የማህበረሰብ ለውጥ ሂደት ቁልፎች 2

ፋኒ ክሮዝቢን ላስተዋውቅዎ! በአሜሪካ ኮንግረስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር ያደረገች ሴት ናት። ስለዚች ሴት ብዙም ሰምታችሁ ላታውቁ ትችሉ ይሆናል። ይህች ሴት ታዋቂውን ‘ብሌስድ አሹራንስ’ ጨምሮ በርካታ ፈጣሪን የሚያመሰግኑ መዝሙሮችን እና ውዳሴዎችን በመጻፍ ተወዳዳሪ የላትም። የካቲት ሁለት ቀን አስራ ዘጠኝ አስራ አምስት ዓ/ም ዘጠና አምስተኛ ዓመት የልደት በዓሏን ለማክበር ከሁለት ወር […]

ነፃነት እና ምግባር፡-የራስ እና የማህበረሰብ ለውጥ ሂደት ቁልፎች

ነፃነት ተድላ ወይም ተወዳጅ ሐሳብ ብቻ አይደለም። የሰው ልጅ ያለ ነጻነት ከቶውንም ሙሉ ‘ሰው’ ነኝ ማለት አይችልም። ነጻነት ደስታን ከሚሰጥ ኹነት እና ጥብቅና ሊቆሙለት ከሚገባ ፅንሰ-ሐሳብ ሁሉ እጅግ ይልቃል። በነፃነት አለመኖር የሚያስገኘው መልካም ነገር ቢኖር መራራ ሕይወት ነው። በነፃነት አለመኖር የሚያስገኘው እጅግ መጥፎው ነገር ደግሞ ሰብዓዊ ክብርን መገፈፍ ነው። መራራ […]

የነጻ ንግድን አስፈላጊነት:የጽሁፍ እና የቪዲዮ ውድድር

የነጻ ንግድን አስፈላጊነትን የሚያሳይ የጽሁፍ እና የቪዲዮ ውድድር የነጻ ንግድን አስፈላጊነት እና ጥቅም ከ2ገጽ ባላነሰ እና ከ3 ገጽ ባልበለጠ ጽሁፍ በመግለጽ ወይም ደግሞ ከ1 ደቂቃ ባላነሰ እና ከ2 ደቂቃ ባልበለጠ ቪዲዮ በመግለጽ ለሽልማት ይወዳደሩ።በሁለቱም ዘርፍ ከ1 እስከ 3 የሚወጡ ተወዳዳሪዎች በአዲስ ዓመት ዋዜማ ይሸለማሉ። ተወዳዳሪዎች እድሜያቸውከ18 እስከ 35 የሆኑ ኢትዮጵያዊያን […]

“ተወዳዳሪ የቴሌፎን ገበያ እንፈልጋለን!” የኢትዮ-ቴሌኮም ጥገትላሞች!

በ21ኛው ክ/ዘመን ለውጭ ገበያ እና ተወዳዳሪ “ገበያህን እና ድንበርህን ዝጋ!” የሚል ሰው ይኖራል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ቢመስልም በሌላም ሃገር ይሁን በኢትዮጵያ የዚያ ዓይነት ሰዎች አሉ። ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሃገር ከምትልከው ምርት የምትገዛው በብዙ እንደሚበልጥ የሚረዳ ሰው የኢትዮጵያን ገበያ ለውጭ ዝግ ይሁን ብሎ አፉን ሞልቶ አይናገርም።ምክንያቱም እነሱ እኛ ላይ ጥገኛ ከሆኑት […]

EduDoc & Fellowship program2018

Centre for Civil Society is proud to declare EduDoc 2018 open! Started in 2015, EduDoc is CCS’s annual international short film competition that brings to life the stories of education – its challenges, achievements and celebrations, through the medium of cinema each year. EduDoc aims to identify and document the […]

ቺሊን የታደጋት የቺካጎ ቦይስ ምክር ለኢትዮጵያ

በታህሳስ ወር 1976ዓ/ም የስዊድን መዲና ስቶክሆልም ጎዳናዎች፣ሻይ ቤቶች፣ምግብና መሸታ ቤቶች ሁሉ የአሜሪካዊያን እና የአሜሪካ ጉዳይ ጎልቶ ይወራ የነበረበት ወቅት ነው። በወቅቱ  ይህን የታዘቡ ሰዎች “ስቶክሆልም የአሜሪካን 200ኛ የነጻነት ዓመት በይፋ እያከበረች ትመስል ነበር።” ብለዋል። በዚያ ዓመት በሰባቱም ዘርፎች የኖቤል ሽልማት ያሸነፉት ሰባቱም ሰዎች አሜሪካዊያን ነበሩ። የስዊድን ሮያል አካዳሚ የኖቤል አሸናፊ […]

የኒዮ ኮሎኒያል ቻርተር ትግበራ ወይስ ነጻ ገበያ? ለኢትዮጵያ የቱ ይበጃል?

የኢኮኖሚ ዕድገት መሰረታዊ መሰረቶች ከተፈጥሮዊ ሕጎች ወይም ከኦሪት ዘመን ትዕዛዛት ይመነጫሉ። አትስረቅ ፣ የሰውን ንብረት አትመኝና በሐሰት አትመስክር ከሚሉት የወጣ ነው። “የሥርቆት” ጨዋታ የሌላን ሰው ሐብት መቀራመት ያመጣል።ሐብትን የማሳደግ ተስፋን ያጨልማል። የሌሎችን ንብረት መመኘት የሌላን ሰው ሐብትን አስገድዶ ለመከፋፈል ድርጊት ይጋብዛል። ይህ ደግሞ የነገውን ምርት የማምረት ተነሳሽነት አደጋ ውስጥ ይከታል። […]

የዶላር ምንዛሬ ዋጋ መጨመር እና የብር ዋጋ ማጣት-ትርጉም እና ምንነት (2) 

የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ይበልጥ ተዳከመ ማለት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ሃገር ዕዳ እንዳለባት ጠቋሚ ምልክት ብቻ ሳይሆን ይሄንንቱ ዕዳ ለመክፈል የምታደርገው ጥረት መንግስትን ተፈታትኖታል ማለት ነው። የብር ዋጋ መውደቅ ማለት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት በአንጻራዊ መልኩ ከጎረቤት ሃገራት አንጻር ወደኋላ እየተጎተተ መሆኑንም ጠቋሚ ነው።