የዶ/ር አቢይ ዕቅድ እና የኢኮኖሚ ነጻነት

  ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንትን ሊስቡ የሚችሉ አሰራሮችን ለማስፋፋት እና እንቅፋቶቹን ለማንሳት የሚረዳ ዕቅድ ነድፈው ወደ ስራ መግባታቸውን ነግረውናል። እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ በትክክል ተጠንቶ ስራ ላይ የሚውል ከሆነ ይህ ዜና ሳይሆን ለኢትዮጵያ ብስራት ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያን አብዛኛው ችግሮች የሚፈታበት ቁልፍ ያለው እዚህ ነው። ቢዝነስ እና […]

የፊስካል ፖሊሲው ክሽፈት፣መራራ ዋጋው እና መፍትሄዎቹ

በኢኮኖሚክስ ሳይንስ የኖቤል ሽልማት ያገኘው የራሽናል ኤክፔክቴሽን ቲወሪ ቀማሪ ሮበርት ሉካስ መንግስት ትክክለኛ ባይሆንም ለፖለቲካ ድጋፍ ህዝቡ የሚፈልገውን ዓይነት(ለኢኮኖሚ ጎጅ እንደሆነም ቢታወቅ እንኳ) ግን መሬት ላይ ካለው የኢኮኖሚ ሃቅ ጋር የማይጣጣም ፖሊሲ የሚተገበርበት ሃገር ድህነት፣ስራ አጥነት፣የኑሮ ውድነት እና ማህበራዊ ምስቅልቅል መገለጫው እንደሚሆን ይገልጣል። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ!

የኢትዮጵያዊው ፈርዖን የኢኮኖሚ መርሆች እና የአስተዳደር ጥበብ

(By Kidus Mehalu)በግብጽ ባለ ሙሉ ስልጣን የነበረው የ26ኛው ስርዎመንግስት ኢትዮጵያዊ ፈርኦን ለየት ያለ የግብር አሰባሰብ መርህ  ነበረው። “ያ መርህ በኔ ዘመን የተሻለ ከሚባለው ከእንግሊዝ የግብር አሰባሰብ ስርዓት የተሻለ ነበር።” ፈረንሳዊው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ሊቅ እና ፈላስፋ ቻርለስ ሉይስ ሞንቴስኪዩ በኢትዮጵያዊያኑ ፈርኦኖች የታሪክና አስተዳደር ድርሳን መመሰጡን ቀጥሏል። “ሰው እንደቤቱ እንጅ እንደ ጎረቤቱ […]

ግብር እና ሞት-3

ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ የድህነት እና የረሃብ ልዩነት ወይም ደረጃ እንዳለው የተረዳው ለረሃብተኞች በተካሄደ ‘የላይቭ ኤድ’ የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ነበር። በወቅቱ ለመላው ዓለም በሚተላለፍ የቴሌቪዥን ስርጭት የሰውን ልጅ አንጀት ለማራራት በችጋር የተጎሳቆሉ የተለያዩ ሃገር ሰዎችን ምስል በቴሌቪዥን ያሳያሉ። ቢሆንም ግን እንደ ኢትዮጵያዊቷ ሕጻን ብርሃን ወልዱ ዓለምን ስለርሃብ የሚያይበትን መነጽር […]

ግብር እና ሞት-2

የአሜሪካ ምስረታ የነጻነት ሰነድ ላይ “መንግስት ለዜጎች የሚሰጠው መብት የለም፤የተቋቋመው ቀድሞውኑ የነበራቸውን መብት ለመጠበቅ ነው።” ይላል። ከዚህ መግቢያ ተነስቼ በቀጥታ ወደ ጥንት ልውሰዳችሁማ። አይ! መግቢያ አያሻኝም የሚል ደግሞ ችግር የለውም ወደፊት እንጅ ወደኋላ ለመሄድ የመግቢያ ክፍያ ስለሌለ የጊዜ ፈረስን በጋራ የኋሊት እንጋልብ። ድሮ….ድሮ…..ድሮ…… እንዲህ ሆነ።አዎ! አሁን እየደረስን ስለሆነ ልጓምዎን ጠበቅ […]

ግብር እና ሞት

መንግስት የዜጎችን ሰላማዊ ህይዎት፣ ነጻነት፣ እና ንብረት የመጠበቅ ግዴታውን ይወጣ ዘንድ ግብር መሰብሰብ ይኖርበታል። ይህ የማይታበል ሃቅ ነው። በግብር መልክ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለተለያዩ የጤና፣ የትምህርት፣ የመከላከያ እና ሌሎች ለህዝብ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የመንግስት ወጭዎችን ለመሸፈን ይውላል። በተጨማሪም ግብር ነጋዴው በገበያ ላይ ለማዋል የማይችላቸውን ወይም ለገበያ ለማቅረብ አዳጋች የሆኑ ህዝባዊ እቃዎችን […]

የመንግስት ወጭ እና የኢትዮጵያዊያን ኪሳራ

የአንድ ሃገር መንግስት የገቢ ምንጭ ከሃገር ውስጥ የሚሰበስበው ግብር ነው። ሆኖም መንግስት በሚሰበስበው ግብር ልክ ዕቅዶችን አውጥቶ ተፈጻሚ ማድረግ ካልቻለ ልክ አንድ ግለሰብ ከገቢው በላይ የሚፈልገውን ወይም የሚያምረውን ነገር ለማድረግ ሲሞክር ችግር እንደሚደርስበት ሁሉ ችግር ይገጥመዋል። ይህን ጊዜ መንግስት ሌላ ገንዘብ ማግኛ ዘዴ ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ወደ አበዳሪዎች ይሄዳል ማለት […]

(By Redeat Bayleyegn)ኢትዮጵያ እና የመንግስት ግዝፈት!

(By Redeat Bayleyegn)ኢትዮጵያ እና የመንግስት ግዝፈት! ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ከአራት ወራት በፊት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገው ነበር:: ስልጠና ቢባል በሚሻለው ስብሰባ ላይ የሚከተለውን ገልፀው ነበር:: እንደ ጠቅላይ ሚንስቴር የመጀመሪያ የስራ ቀናቸው ዕለት ጠረጴዛቸው ላይ የ120 ሰዎች ውጭ ሃገር ሄዶ ለመታከም ማመልከቻ ጠብቋቸዋል:: የመጏጏዣ ቲኬትን አያጠቃልልም:: የነዚህ 120 ሰዎች […]

(By Redeat Bayleyegn) የመጀመሪያው መሬት ለአራሹ እና መዘዙ

(By Redeat Bayleyegn) የመጀመሪያው መሬት ለአራሹ እና መዘዙ ደርግ ለአመታት የቆየውን የ”መሬት ለአራሹ” ጥያቄ በታህሳስ 1967 በአዋጅ “መፍትሄ” ሰጠሁበት አለ:: መፍትሄውም የኢትዮጵያ መሬትን ከግል እና መንግስታዊ ካልሆነ ባለቤትነት ወደ መንግስት ወይም በተለምዶ የህዝብ ባለቤትነት ለወጠው:: ኢትዮጵያ በዘመኗ (ሺዎች) አይታው የማታውቀው ይህ የመሬት ይዞታ 44 አመት ሊሆነው ነው:: በኔ አመለካከት ውጤቱም […]