⦿የዶላር ምንዛሬ ዋጋ መጨመር እና የብር ዋጋ ማጣት-ትርጉም እና ምንነት 1 

(By Kidus Mehalu/በቅዱስ መሐሉ ©2017) የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብር ከዶላር አንፃር ያለው የምንዛሬ ዋጋ በይፋ እንዲቀንስ ማድረጉ ይታወቃል።ይህን ያደረገበት ምክንያት ደግሞ ምርታቸውን ወደ ውጭ ሃገር የሚልኩ ነጋዴዎች/ኤክስፖርተሮች/ በውጭ ሃገር ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና ምርታቸውን በቅናሽ ዋጋ ለማቅረብ እንዲችሉ ማስቻል የሚል ነው።ሆኖም ግን የኢትዮጵያን ኤክስፖርተሮችን ለማበረታታት በሚል ምክንያት የብር ዋጋ […]

የዓለም ኢኮኖሚ ነጻነት እና ኢትዮጵያ 

(By Kidus Mehalu)  የካናዳው ፍሬዘር ተቋም እና የዓለም የኢኮኖሚ ነጻነት ኔትወርክ በየአመቱ የሚያወጣውን ሪፖርት ከሰዓታት በፊት ይፋ አድርጓል።  ሪፖርቱ 159 ሃገራትን ያካተተ ሲሆን ኢትዮጵያ በዘንድሮው ሪፖርት አምና ከነበረችበት የ145ኛ ደረጃ ወደታች አንድ ደረጃ ዝቅ በማለት የ146ኛ ደረጃን አግኝታለች።  ሆንግ ኮንግ እንደ ሁሌውም የአንደኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን ሲንጋፖር፣ ኒውዚላንድ፣ ስዊዘርላንድ፣ አየርላንድ፣እንግሊዝ፣ […]

ዘረኞች የፈነጠዙበት፤ዴሞክራቶች የተሸማቀቁበት የጀርመን ምርጫ! 

የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራቲክ ሕብረት ፓርቲ የዕሁድለቱን ምርጫ 33በመቶ በሆነ ድምጽ አሸንፏል። ይህም የሃገሪቱን ቻንስለር አንጌላ መርክልን ለአራተኛ ጊዜ ጀርመንን እንዲመሩ ዕድል ሰጥቷቸዋል። በጀርመን ፖለቲካ ውስጥ ጠንካራ ሆኖ የቀጠለው የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ፓርቲ ምርጫውን ቢያሸንፍም ያገኘው ውጤት ግን ከአራት ዓመታት በፊት ካገኘው 8በመቶ ያነሰ ነው። እስከዛሬ ጀርመንን ከክርስቲያን ዴሞክራቶች ጋር  በጥምረት ሲመራ […]

አንስታይን፣አሜሪካ እና ጃፓን:-የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ!

(By Kidus Mehalu) እኤአ ከ1894ዓ/ም እስከ 1895ዓ/ም በጃፓን እና በቻይና በተደረገው ጦርነት በአውሮፓዊያን ይሰለጥን የነበረው የቻይና ሰራዊት ክፉኛ ተመቶ ጃፓን በቢጫ ባህር እና በኮሪያ ላይ ከመንገሷም ታይዋንን ተቆጣጠረች። ይህም አልበቃ ብሏት በቻይና እና ራሽያ መሃል የሚገኘውን ስትራቴጅክ ቦታን በእጇ አደረገች። ይህ ቦታ ማንቹሪያ ይባላል። ሩሲያ “ማንቹሪያ የቻይና ነው” በማለት በ1904 ከጃፓን […]

ወተት  የሚጡት ዝሆኖች — የንብረት ባለቤትነት መብት እና የአካባቢ ጥበቃ!

(By Kidus Mehalu) የንብረት ባለቤትነት መብት መረጋገጥ ለአካባቢ እንክብካቤ እና የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅ ረገድ ወሳኝ እና የማይተካ ሚና ይጫወታል። እንዴት የሚለውን በዝርዝር እንመልከት። እስከ አስራ ዘጠኝ ዘጠና ዓ/ም ናሚቢያ የምትገዛው ደቡብ አፍሪካን ጠፍንጎ በያዘው በዘረኛው የአፓርታይድ ስርዓት ነበር። የናሚቢያ ዜጎች የኔ የሚሉት ነገር አልነበራቸውም። ህይዎታቸው፣ ንብረታቸው፣የዱር አራዊቱ ሁሉ የአፓርታይድ አርክቴክቶች […]

ወርቅ፣ዶላር እና አሜሪካ!  (ክፍል 2 እና የመጨረሻ ክፍል) 

(©Kidus Mehalu) እኤአ ነሃሴ 15 ቀን 1971 ዓ/ም ከገንዘብ ሚንስትራቸው ጆን ኮናሊ፣ የብሄራዊ ባንኩ ሊቀመንበር አርተር በርንስ እንዲሁም ከኢኮኖሚ እና ገንዘብ ጉዳዮች አማካሪዎቻቸው ሄርበርት ስቴይን እና ፖል ቮከር ጋር ሆነው በጉዳዩ ላይ በካምፕ ዴቪድ ሲመክሩ የዋሉት ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ምሽቱን በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው ዓለም ለአጭር ደቂቃ ጆሮ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ […]

ወርቅ፣ዶላር እና አሜሪካ!

(©Kidus Mehalu) ወርቅ ድንበርና ዜግነት ሳይወስነው በመላው ዓለም ተፈላጊ መሆኑ፣ ፖለቲከኞች እንደ ወረቀት ገንዘብ በፈለጉ ጊዜ ስለማያጋሽቡት፣ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ቀላል እና በተፈለገው መጠን መስራት የሚቻል መሆኑ፣ ለብዙ ጊዜ ቢቀመጥ የማይበላሽ እና ዋጋውን ጠብቆ መቆየት የሚችል መሆኑ፣እንዲሁም በቀላሉ የሚተጣጠፍ፣ ጠንካራ እና እንደ ወረቀት ገንዘብ በማቃጠል ፈፅሞ ማጥፋት የማይቻል መሆኑ እውነተኛ ገንዘብ […]

የሰዎች ተፈጥሮ፣ጤናማ ኢኮኖሚ እና መንግስት

(Kidus Mehalu) የኢኮኖሚ ጤናማነት ማሳያ ግለሰቦች በነጻ የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ያላቸው ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። በተፈጥሮ ተሰጥኦዎቻችን እና ችሎታዎቻችን የተለያየን ነን። አንዳንዶች ከሌሎች የላቀ ተሰጥኦ አላቸው። የአንዳንዶች ተሰጥኦ ትልቅ እሴትን የሚፈጥር ነው። አንዳንዶች ያላቸውን እጅግ የላቀ ተሰጥኦ ሳያውቁት ዕድሜያቸው ይሄዳል። ከነጭራሹ ተሰጥኦዎቻቸውን ሳያውቁ የሚያልፉም ሞልተዋል። ሰዎች በአይምሯቸው፣ በጥንካሬያቸው፣ በጉልበታቸው እና በመጠናቸው […]